A Bit About Us

GELILA INTERNATIONAL SEMINARY is a non-profit organization licensed by the Ethiopian Government- Ministry of Peace in 2007G.C.

GELILA INTERNATIONAL SEMINARY offers programs which are highly spirit filled and are geared towards equipping and empowering leaders who will change their nation and the world at large.

Our Best Programs

Our courses are relevant to the 21st Century leaders, Business men, counselors and social workers, and are an effective aid to the development of all Christian believers in Ethiopia.

The Doctor of philosophy Program offers Leaders and ministers an opportunity for professional and personal growth. It is a postgraduate qualification which exposes the post graduate student to advanced coursework and dissertation with the focus on large corporate organizations and Mega institutions. This course is designed for leaders and higher position specialists to expand their knowledge, good judgment, skills, attitude and experience and examine a large Christian organizational problem in depth.

The program has advanced concepts for each disciplines.. Students will become conversant in best organizational practices, understand how to do applied research, and implement strategic thinking to impact their own ministry context. The program includes an integral field-based component that provides students with an opportunity to develop or create bold new leadership endeavors that will have practical impact on ministry.

This program equip the student to integrate Christian principles into critical thinking and decision-making in one’s personal and/or professional life; and also Give the student a working knowledge to meet the needs of diverse audiences/targeted age groups and organizational settings; Equip the student the practice of leadership and management, counseling and social work.

Enrolment Process

Students can start studying at new academic intakes only 3 times during the year April, August and December. They can graduate once in the academic year. Gelila International Seminary will hold central graduations ceremonies each year throughout Ethiopia. Certificates, Diplomas and Degrees will be forwarded to students on completion of their studies

Board
Members

Experienced and well matured board members who leads Gelila. 

10 +
Years
1000 +
Graduates
15 +
Awards
155 +
Courses
6 +
Departments

What's happening

Latest news and updates

ስለእኛ ምን አሉ?

በኮሌጁ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ ያስተዋልኩዋቸውን ነገሮች ለመግለጽ ሳስብ በእውነት ጌታን እጅግ አድርጌ አመሰግናሁ፡፡ ምክንያቱም አንዱና ዋነኛው አስፈላጊ ነገር የመንፈሳዊ ህይወት ስብዕና ግንባታ ነው፡፡ እኔ በራሴ ለመንፈሳዊ ህይወቴ ትልቅ ነገር ያገኘሁበት ብዙ የተጠቀምኩበት ቤቴን የለወጥኩበት እራሴን የቀየርኩበት እንደገና ደግሞ ለአገልግሎቴ ትልቅ መሰረት የሆነኝ ትምህርት ነው ያገኘሁበት፡፡ በተለይም ገሊላ ሴሚናሪን ሳነሳ ሁልግዜ እላለሁ እኔ የወሰድኳቸውን ኮርሶች አውቃቸዋለሁ 17 ኮርሶች ናቸው የወሰድኩት ግን ይገርምሀል እኔ 18 ኮርስ ነው የወሰድኩት ማለት እችላለሁ የዶ/ር ጥላዬ የሴሚነሪው ፕሬዝዳት ህይወት 18ተኛ መፅሀፍ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ በአጠቃላይ ላይፉ ፍቅር ከ…. እኔ እንደ አገልጋይነቴ ስለ ፍቅር ብዙ ሰብኬ አውቃለሁ ስለፍቅር ተምሬም አውቃለሁ ነገር ግን ፍቅር በመፅሀፍ መልክ መፅሀፍ አይንቀሳቀስም አይደል ግን የሚንቀሳቀስ ህይወት አግኝቻለሁ፡፡ ህይወቱ ይናገራል ቃል በተግባር ሲገለጥ አይቻለሁ፡፡ 18ተኛ ኮርስ (የተገለጠ የህይወት ምስክርነት ያለበት) ወስጄ ነው የጨረስኩት እና በጣም የተለወጥኩበትና ህይወቴ የተቀየረበት ሥፍራ ነው፡፡ በአጠቃላይ በኮሌጁ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ እጅግ በጣም ብዙ ጠቃሚ የሆነ ነገር ተምሬያለሁ በቀጣይ ደግሞ ብዙ አደራ አለብኝ ያው እንደምታየው አደራ ሰጥተውኛል እና በቅድስና ለመኖር 'የክርስቶስን ህይወት በቀሪው ህይወቴ በደንብ ኖሬ በማሳየት በትውልዱ መካከል መገለጥ እፈልጋለሁ መፅሀፍ ቅዱስ በፊሊ 2፡5 ላይ ”በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ ሀሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን” ይላል፡፡ እየሱስ ውስጥ የነበረው ሀሳብ እኔ ውስጥ ደግሞ አንዲገለጥና ለትውልድ ጥሩ ምሳሌ ሆኜ ኖሬው ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡

ፓር ዳዊት ደጀኔ (ዶር)
ፓ/ር ዳዊት ደጀኔ (ዶ/ር) የኮሌጁ ተመራቂ (ተሸላሚ)

እዚህ ኮሌጅ ውስጥ በመማሬ ያገኘሁት ነገር እውቀት ብቻ አይደለም ማለትም ነገሮችን ማብራራት ወይም ደግሞ የተቀመጡ ቲዮሪዎችን እንዲህ ነው ብሎ መተንተን ብቻም ሳይሆን ከዚያ ያለፈ ህይወትን የሚሠራና የሚቀይር ነገር ነው፡፡ ምክኒያቱም እነዛን የተቀመጡትን መረጃዎችና እውቀቶችን ያስተማሩን በህወታቸው የኖሯቸው experience ያደረጓቸው ሰዎች ስለሆኑ እውቀት ብቻ ሳይሆን ህይወትና ጥበብንም ጭምር ነው፡፡ ጥበብ ከእውቀት የሚለየው ነገሮችን በምን ግዜ በምን ቦታ ምን ማድረግ እንዳለብን እንድናውቅ የሚረዳን በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው የምንማረውን ነገር /የተማርነውን መረጃ/ በህይወታቸው የተለማመዱና ይህን ተሞክሯቸውን ማካፈል ሚችሉ ሰዎች ሲያስተምሩን ነው ብዬ አምናለሁ ስለዚህ እኔም የእነሱን ተሞክሮ ማግኘቴና መካፈሌ የተለየ ነገር በህይወቴ ጨምሮልኛል የምለው ይሄንን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኮሌጁ ያዘጋጃቸው የመማሪያ ግብአቶቹ መሳሪያዎቹ ማቴሪያሎቹም ሁሉ ለማንበብ ለመረዳትና ለመጠቀም ቀላል ተደርገው የቀረቡ መሆናቸውን አይቻለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች ናቸው እንግዲህ ኮሌጁን በጣም እንድወድና የተለየ ነው እንድል የደረገኝ እንዲሁም የተማርኩትን ትምህርት እንድኖርበትና ሌሎችንም እንዳስተምርበት ትልቅ ስንቅ ሆኖኛል፡፡

ዳዊት መስቀሉ
ዳዊት መስቀሉ የኮሌጁ በዲግሪ የማዕረግ ተመራቂ

በገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪ ውስጥ እጅግ በጣም ትልልቅ ልምድና እውቀት ያላቸው ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች እንዲሁም የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሱ በስነምግባር የታነፁ ሰራተኞች ያሉበት ተቋም እንደሆነ አይቻለሁ፡፡ በዚህ ኮሌጅ ውስጥ መማር በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ ህይወት ማንነትን የሚገነባ እጅግ ጠቃሚ ትምህርት እንደሆነ አይቻለሁ፡፡ በዓለም ደረጃ Leadership and management የሚወስዱ ሰዎች የተማሩትን ሁሉንም ኮርሶች globally out standard ተደርገው የሚሰጡትን ሙሉ በሙሉ ወስደናል፡፡ ከዛ በተጨማሪ ደግሞ ክርስቲያናዊ ስራ አመራር ምንድን ነው የሚመስለው የሚለውን ነገር በትክክል በተግባር ያየንበት በተለይም ከትምህርቱ በላይ የሚያስተምሩትን ነገር በህይወታቸው የሚገልፁና ለኛም ምሳሌ የሚሆኑ የትልቅነት መለኪያና ሚዛን የሚሆኑ ትልልቅ ሰዎችን አግኝተናል፡፡ በእነርሱ እግር ስር ሆኖ መማር እጅግ ያስደስታል፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ የተለያዩ አማራጮች ስለነበሩት ብዙ የጥናትና ምርምር ፅሁፎች የማቅረብ እድሎች ነበሩን ሴሚናሮችን የመካፈል እድሎች ነበሩን' በክፍል ውስጥ ቁጭ ብሎ የመማር እድሎች ነበሩን ምንም እንኳን የCovid ወረርሽኝ ከፍተኛ ስጋት የነበረበት ግዜ ቢሆንም መምህራኖቻችን በቻሉት አቅም ሁሉ እኛን ለማገዝ እና ለመርዳት የሚተጉ ምሳሌ ሆነው ማስተማር የሚፈልጉ ናቸው፡፡ እኔ ያልኩትን ሳይሆን የማደርገውን አድርጉ ብለው በድፍረት ማስተማር የሚችሉ በስነምግባር የታነፁ ሰዎች ያሉበት ተቋም ነው፡፡ እኛም ደግሞ ስኬታማ ግዜ ያሳለፍንበት በእውቀት በክህሎትና በአመለካከት የተቀረፅንበት የታነፅንበትና ለወደፊት ህይወታችን መሰረት የሚሆን ትልልቅ ጡቦች ያስቀመጥንበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ተቋም ውስጥ መማር ብቻ ሳይሆን ማገልገልም ጭምር የምትመኝበት ነው፡፡ ትልልቅ ተቋሟት ውስጥ ትልልቅ ደሞዝ ይከፈልህ ይሆናል እኔም ከእንደዚህ አይነት ተቋም ነው የመጣሁት ከዛ በላይ በነፃ ላገለግል የምትልበት ቤትና እንደዚህ አይነት ሰራተኞች ያሉበት ገራሚ ተቋም እንደሆነ ነው ያሁት፡፡

ምስክር ገበየሁ
ምስክር ገበየሁ የኮሌጁ የዶክተሬት ዲግሪ የማዕረግ ተመራቂ

ከሁሉ አስቀድሜ የዚህ ራዕይ ባለቤትና መስራች የሆነውን እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ በመቀጠል ደግሞ ይህን ራዕይ ተቀብለው በኢትዮጵያ ምድራችን ላይ የመጡትን ገሊላ ሴሚናሪን እግዚአብሔር ዘመናቸውን ይባርክ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ገሊላ ሴሚናሪን ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል ምክንያቱም የብዙ ትውልድ አዕምሮ የሚቀረፅበት መሆኑን መመስከር እችላለሁ ምክኒያቱም ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በማስተማርና እና ብዙ ጊዜ ደግሞ አብሬ በማስመረቅ እንዲሁም በመማርም ጭምር እግዚአብሔር እድል ሰጥቶኝ ለማየት ችያለሁ፡፡ እኔ መናገር የምፈልገው ኮሌጁ በጥሩ ዝግጅትና አደረጃጀት የመጣ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ የተነሳና በሰዎች ዕውቀት ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ጠንካራ መሪ፤ ብቁ መምህራን፤ ታታሪ ሠራተኞችና በቂ የትምህርት ግብዐት ያለው ተመራጭ ኮሌጅ መሆኑን ነው፡፡ በአጠቃላይ ያስተዋልኩት ነገር የምር መለወጥ የሚፈልግና በመንፈሳዊ ክህሎት ራሱን ማብቃት የሚፈልግ ሰው ጊዜ ሳያጠፋ ወደ ገሊላ ሴሚናሪ በመሄድ እንዲማር እመክራለሁ፡፡

ተስፋዬ ደገሳ (ዶ/ር) የዶክተሬት ዲግሪ ተመራቂ

ገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪ የመጣሁት በኤልሻዳይ ቴሌቨዥን ማስታወቂያው ሲተላለፍ ተመልክቼ ነው፡፡ ከዚያም ከጋደኛዬ ጋር መጥተን እኔ ወዲያውኑ ተመዝግቤ መማር ስጀምር እርስዋ ደግሞ ከሁለት ዓመት በኋላ መማር ጀምራለች፡፡ ከኮሌጁ ሠራተኞች ስጀምር በጣም ትሁቶችና ተባባሪ ናቸው የምንፈልገውን ነገር እና ጥያቄም ሲኖር ወዲያው ነው ምላሽ የሚሰጡን እና ጥሩ የሆነ አቀባበል አላቸው፡፡ የአስተማሪዎቹ የትምህርት አሰጣጥና አቀራረብም አጅግ የሚያበረታታ ነው፡፡ እኔ የምከታተለው የርቀቱን ትምህርት እንደመሆኑ ትምህርቱ ግልፅ የሆነ እና የሚያስተምሩበት መንገድ ለመረዳት ቀላል የሆነ አቀራረብ ነው በአጠቃላይ የማስተማሪያ ሞጁሎቹንም ወድጄዋለሁ በጥንቃቄ እንደተዘጋጁ አስተውዬአለሁ፡፡ ለሌሎችም ሰዎች የምመክረው ወደዚህ ትምህርት ቤት እንዲመጡና እንዲማሩ ነው፡፡ ትምህርቱ ለአገልገሎት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው ከዚህ ኮሌጅ በምናገኘው ትምህርት ለሌሎች የሚተርፍና የሚለውጥ አገልግሎት መስጠት ከመቻላችን በተጨማሪ የግል ህይወታችንም ለመገንባት ጭምር የሚጠቅም ነውና ወደዚህ ትምህርት ቤት እንዲመጡ አበረታታለሁ፡፡ ኮሌጁ የሚገኝበት ቦታ ደግሞ ለትራንስፖርት ምቹና ቀላል center የሆነ ቦታ ነው፡፡

ዮሴፍ ክፍሌ የኮሌጁ በዲግሪ የማዕረግ ተመራቂ

Need more
information?

Just drop us your message