- 9720
- +251 948 50 50 50/ +251 986 50 50 50
- info@gelilaseminary.com
- Megenagna Metebaber Bldg. 5th fl, Addis Ababa
Gelila International Seminarium College
ለድንቅ እና ጥልቅ አላማ በጥር ወር 2013 ዓ.ም የተመሠረተው “የገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪየም ሁሉን አቀፍ የባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ”
ከዚህ በተጨማሪ ካውንስሉ በባለሙያዎች ስብስብ እና ከሴሚናሪው ቦርድና ከማኔጅመንቱ ጋር በመሆን ችግር ፈቺ የሆኑና በጥናትና ምርምር የተደገፉ ስራዎችን በማከናወን ጤናማ/ ሰላማዊ የስራ ትብብርና የዓላማ አንድነት ድልድይ ሆኖ የማገልገል ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ቀዳሚና ተምሳሌታዊ የሆነ ሥራን ይሠራል
የምስራቹን ወንጌል ለትውልዱ ለማድረስ ሲሉ በነፍሳቸው ተወራርደው ቦታና ጊዜ ሳይገድባቸው በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ ዘመናቸውን በሙሉ በጽናት ያገለገሉ በርካታ አንጋፋ የወንጌል አርበኞች ለነገዬ ብለው ያስቀመጡት ጥሪት ባለመኖሩ ምክኒያት ዛሬ ያለጠዋሪና ደጋፊ በየስፍራው ተረስተው ይገኛሉ፡፡ ታዲያ ኮሌጃችን እነዚህን አንጋፋ የወንጌል አርበኞች መደገፍ ለትውልዱ ምሳሌ ሆኖ ከማስተማሪያነቱ በተጨማሪ በቀረው የዕድሜ ዘመናቸው በትውልዱ አዝነውና ከሚያልፉ ይልቅ ትውልዱንና ምድሪቱን ባርከው ወደ እረፍታቸው ቢሄዱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያምናል፡፡
በመሆኑም ኮሌጃችን ይህንን ኃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በሁለት ዓይነት መንገድ የእነዚህን አንጋፋ የትውልድ መሠረቶች ችግር ለመቅረፍ ይሠራል፡፡ ይኸውም
ይህ ታላቅ ራዕይ እውን የሚሆነው በኮሌጃችንና በኮሌጁ ማህበረሰብ ጥረት ብቻ ሳይሆን የአምላካችን የእግዚአብሔር ኃሳብ የገባቸውና የቃሉ እውነት የበራላቸው ሁሉ ያገባኛል ብለው ኃላፊነት ሲወስዱና የየበኩላቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ በመሆኑ የዚህ ድንቅ ዓላማ አስፈጻሚ በመሆን በሚችሉት ሁሉ በምክርዎ፤ በሞያዎ፤ በጉልበትዎ፤ በገንዘብዎ፤ በቁሳቁስና በጸሎትዎ ከጎናችን በመቆም እንዲደግፉን እናበረታታለን፡፡
ኮሌጃችን የቤተ ክርስቲያን መሠረቱ ቤተሰብ እንደሆነ ስለሚያምን በቤተሰብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ የበርካቶችን ትዳር ከመፍረስና ቤተሰብን ከመበተን ያድናል ብሎ ስለሚያስብ በዚሁ ላይ መሠረት ያደረገ የቤተሰብ መማክርት ማዕከል በማቋቋምና ባለሞያዎችን በማሰልጠን እንዲሁም ሰፊ የምክር አገልግሎት በመስጠት የብዙዎችን ቤተሰብ ከመፍረስና ከመበተን ለማዳን አበክሮ ይሠራል፡፡
ጠንካራ ቤተክርስቲያን የጠንካራ ቤተሰቦች ስብስብ መሆንዋ እሙን ነው፡፡ በተጻራሪው ደግሞ በቤተሰቦች ላይ ጠንክራ ያልሰራች ቤተ ክርስቲያን በብዙ ችግሮች ውስጥ ስታልፍና ጸንቶ መቆም ሲያቅታት ይታያል፡፡ ኮሌጃችን ይህን ችግር ለመቅረፍና በሃገራችን በሚገኙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እና የእግዚአብሄር ቤተሰቦች ላይ በመስራት በጎ ተጽእኖ ለማምጣት በኮሌጁ ውስጥ አንድ የቤተሰብ መማክርት ማዕከል በመክፈትና በበቁ ባለሞያዎች በማደራጀት ለሁሉም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን (ዲኖሚኔሽን) በእኩል አገልግሎት በመስጠት ዓይነተኛ ለውጥ ለማምጠት ከመስራት ጎን ለጎን በዚሁ ዘርፍ ብቁ ባለሞያዎችን ለማፍረት በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እያስተማረ ያስመርቃል፡፡
ታዲያ ይህም ራዕይ ደግሞ ያለርስዎ እገዛ የማይታሰብ ነውና የበኩልዎትን ድጋፍና አስተዋጽኦ ለማበርከት ከጎናችን እንዲቆሙ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን፡፡