"Go therefore and make disciples of all the nations"

የካውንስሉ አላማና ተግባር

ለድንቅ እና ጥልቅ አላማ በጥር ወር 2013 ዓ.ም የተመሠረተው “የገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪየም ሁሉን አቀፍ የባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ”

የሰሜናሪ/ ኮሌጁን ራዕዩንና ተልዕኮውን' ክብሩንና መልካም ስሙን እድገቱንና ግቡን በሁለንተናዊ መልኩ መደገፍ
የሴሚናሪውን ሞኒተሪ (monetary) ፖሊሲ በእቅዱ መሰረት እንዲሰራ ሞያዊ እገዛ ማድረግ
የሴሚናሪውን መልካም እድሎቹንና ፓሊሲዎቹን እንዲሁም መመሪያዎቹን በእውቀትና በሙያ ማጠናከር
ለተቋሙ ውሳኔ ሰጪ እና ፓሊሲ አዘጋጅ/ አቅራቢ አካል በምርምር በጥናትና በሙከራ የተደገፈ ተመራጭ የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀትና በማቅረብ መደገፍ
ተቋሙ የሥራና የአገልግሎት አካባቢውን (working environment) በየጊዜው እያሻሻለ ከፍተኛ የእድገት ደረጃውን ስታንዳርድ ጠብቆ ወደ ከፍታው እንዲጓዝ ሙያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
ሴሚናሪው እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጭምር ከሚያደርጉአቸው ጥረቶች ጋር አካልና ቤተሰብ በመሆን የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለመጠበቅ ነፍሳትን ለማዳን ሕዝባችንንና ምድራችንን በፅድቅ ለማገልገል የሚደረገውን ጥረት የደግፋል
ካውንስሉ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አጫጭር ኮርሶችንና ስልጠናዎችን ምርምሮችንና የልምድ ልውውጦችን በማካሄድ፤ ለሴሚናሪው እድገትና ፍሬያማነት' የሚያበቃ የፈጠራና የአዳዲስ ግኝቶች/creative and innovative ስልት/ ዘዴ በመጠቀም የተቋሙን ከፍታ ለማስጠበቅ ሙያዊ እገዛ ያደርጋል
በሁሉም የሴሚናሪው የትምህርት ፕሮግራሞች በየአመቱ እየተቀበለ የሚያስተምራቸውና የሚያዘጋጃቸው ተማሪዎች ጥራት ባለው ሁኔታ የተማሪዎችን አካዳሚክ እና መንፈሳዊ ከፍታ (Academic Excellence) እያስጠበቀ በየዓመቱ እንዲያስመርቃቸው ያልተቆጠበ/ ያልተገደበ ሙያዊ እና ማቴሪያላዊ ትብብር በማድረግ ረገድ ኃላፊነትን ይወጣል
እንደ እግዚአብሔር ቃል የዘመናችን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ግኝቶችንና ጥበባት በረቀቁበት በአሁኑ ወቅት ዘመኑን ለመዋጀት ምድሪቱን በወንጌል ኃይል የሚወርሱትንና በታላቅ ስሙ የሚፈወሱትን የኢየሱስ ወታደሮችንና የመንግስቱ አምባሳደሮችን በሰማያዊና ምድራዊ (መንፈሳዊና ስጋዊ) ከፍተኛ ትምህርት' እውቀትና ጥበብ በጥልቀት እየመረመሩ መንፈሳዊ ኃይል እንዲታጠቁ ይረዳል
በተለያዩ ዓለማት የማኅበረሰብ አደረጃጀቶች እንደሚታየው ሁሉ የገሊላ ሴሚናሪ ኮሌጅ ባለሙያዎች ካውንስል የራሱን ህልውና አስጠብቆ ራዕዩንና ዓላማውን ከዳር ለማድረስ ብሎም የተቋሙን (የሴሚናሪውን) ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞቹን በፋይናንስ መደገፍ እንዲቻል ጤናማና ህጋዊ የሆነ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን እየተጠቀመ እስከ ፈንድሬዚንግ (fund raising) እና ከዚያም በላይ ስልቶችን እየቀየሰ ውጤታማ አካልነቱንና አንድነቱን ማረጋገጥ ይሆናል

ከዚህ በተጨማሪ ካውንስሉ በባለሙያዎች ስብስብ እና ከሴሚናሪው ቦርድና ከማኔጅመንቱ ጋር በመሆን ችግር ፈቺ የሆኑና በጥናትና ምርምር የተደገፉ ስራዎችን በማከናወን ጤናማ/ ሰላማዊ የስራ ትብብርና የዓላማ አንድነት ድልድይ ሆኖ የማገልገል ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ቀዳሚና ተምሳሌታዊ የሆነ ሥራን ይሠራል

የገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪየም የባለሙያዎች ካውንስል

የምስራቹን ወንጌል ለትውልዱ ለማድረስ ሲሉ በነፍሳቸው ተወራርደው ቦታና ጊዜ ሳይገድባቸው በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ዋጋ እየከፈሉ ዘመናቸውን በሙሉ በጽናት ያገለገሉ በርካታ አንጋፋ የወንጌል አርበኞች ለነገዬ ብለው ያስቀመጡት ጥሪት ባለመኖሩ ምክኒያት ዛሬ ያለጠዋሪና ደጋፊ በየስፍራው ተረስተው ይገኛሉ፡፡ ታዲያ ኮሌጃችን እነዚህን አንጋፋ የወንጌል አርበኞች መደገፍ ለትውልዱ ምሳሌ ሆኖ ከማስተማሪያነቱ በተጨማሪ በቀረው የዕድሜ ዘመናቸው በትውልዱ አዝነውና ከሚያልፉ ይልቅ ትውልዱንና ምድሪቱን ባርከው ወደ እረፍታቸው ቢሄዱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያምናል፡፡

በመሆኑም ኮሌጃችን ይህንን ኃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በሁለት ዓይነት መንገድ የእነዚህን አንጋፋ የትውልድ መሠረቶች ችግር ለመቅረፍ ይሠራል፡፡ ይኸውም

ይህ ታላቅ ራዕይ እውን የሚሆነው በኮሌጃችንና በኮሌጁ ማህበረሰብ ጥረት ብቻ ሳይሆን የአምላካችን የእግዚአብሔር ኃሳብ የገባቸውና የቃሉ እውነት የበራላቸው ሁሉ ያገባኛል ብለው ኃላፊነት ሲወስዱና የየበኩላቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ በመሆኑ የዚህ ድንቅ ዓላማ አስፈጻሚ በመሆን በሚችሉት ሁሉ በምክርዎ፤ በሞያዎ፤ በጉልበትዎ፤ በገንዘብዎ፤ በቁሳቁስና በጸሎትዎ ከጎናችን በመቆም እንዲደግፉን እናበረታታለን፡፡

የቤተሰብ (ትዳር) የምክር አገልግሎት

ኮሌጃችን የቤተ ክርስቲያን መሠረቱ ቤተሰብ እንደሆነ ስለሚያምን በቤተሰብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ የበርካቶችን ትዳር ከመፍረስና ቤተሰብን ከመበተን ያድናል ብሎ ስለሚያስብ በዚሁ ላይ መሠረት ያደረገ የቤተሰብ መማክርት ማዕከል በማቋቋምና ባለሞያዎችን በማሰልጠን እንዲሁም ሰፊ የምክር አገልግሎት በመስጠት የብዙዎችን ቤተሰብ ከመፍረስና ከመበተን ለማዳን አበክሮ ይሠራል፡፡

ጠንካራ ቤተክርስቲያን የጠንካራ ቤተሰቦች ስብስብ መሆንዋ እሙን ነው፡፡ በተጻራሪው ደግሞ በቤተሰቦች ላይ ጠንክራ ያልሰራች ቤተ ክርስቲያን በብዙ ችግሮች ውስጥ ስታልፍና ጸንቶ መቆም ሲያቅታት ይታያል፡፡ ኮሌጃችን ይህን ችግር ለመቅረፍና በሃገራችን በሚገኙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እና የእግዚአብሄር ቤተሰቦች ላይ በመስራት በጎ ተጽእኖ ለማምጣት በኮሌጁ ውስጥ አንድ የቤተሰብ መማክርት ማዕከል በመክፈትና በበቁ ባለሞያዎች በማደራጀት ለሁሉም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን (ዲኖሚኔሽን) በእኩል አገልግሎት በመስጠት ዓይነተኛ ለውጥ ለማምጠት ከመስራት ጎን ለጎን በዚሁ ዘርፍ ብቁ ባለሞያዎችን ለማፍረት በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እያስተማረ ያስመርቃል፡፡

ታዲያ ይህም ራዕይ ደግሞ ያለርስዎ እገዛ የማይታሰብ ነውና የበኩልዎትን ድጋፍና አስተዋጽኦ  ለማበርከት ከጎናችን እንዲቆሙ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን፡፡